በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም አሌክሳንደር ዶልጋኖቭ

ሚያዝያ 4, 2024 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 9, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ‘ከምንም በላይ አስፈላጊው ነገር ከይሖዋ ጋር ያለኝ ወዳጅነት ነው’

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ታሰረ | ‘ከምንም በላይ አስፈላጊው ነገር ከይሖዋ ጋር ያለኝ ወዳጅነት ነው’

ሚያዝያ 8, 2024 በሳማራ ክልል፣ በቶልያቲ ከተማ የሚገኘው የአቭቶዛቮድስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም አሌክሳንደር ዶልጋኖቭ ጥፋተኛ ነው በማለት የሦስት ዓመት እስራት በይኖበታል። ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወደ እስር ቤት ተወስዷል።

አጭር መግለጫ

አሁን የምንኖርበት ዘመን “ቀኖቹ ክፉዎች ስለሆኑ” እንደ አሌክሳንደር ሁሉ እኛም ጊዜያችንን በጥበብ ለመጠቀም ቆርጠናል።​—ኤፌሶን 5:15, 16

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 16, 2023

    ቤቱ ተፈተሸ። ጣቢያ ተወሰደ

  2. ግንቦት 17, 2023

    ከጣቢያ ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ። ስልክ ወይም ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ታገደ

  3. ነሐሴ 10, 2023

    ከቁም እስር ተፈቶ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  4. ኅዳር 13, 2023

    ክሱ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ