በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ፍቅር ከራሳችን ይልቅ የሌሎችን ፍላጎት እንድናስቀድም ይገፋፋናል

ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ለሌሎች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ሁላችንም የመጀመሪያው ሰው የአዳም ዘሮች በመሆናችን አንድ ቤተሰብ ነን ሊባል ይችላል። የአንድ ቤተሰብ አባላት ይዋደዳሉ እንዲሁም ይከባበራሉ፤ በዛሬው ጊዜ ግን እንዲህ ያለው ፍቅር ብርቅ ሆኗል። የሚወደን አምላካችን እንዲህ እንዲሆን አይፈልግም።

ቅዱሳን መጻሕፍት ስለ ፍቅር ምን ይላሉ?

“ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።”—ዘሌዋውያን 19:18

“ጠላቶቻችሁን ውደዱ።”—ማቴዎስ 5:44

ባልንጀራችንን መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው?

አምላክ ፍቅርን በተመለከተ በቃሉ ውስጥ ምን እንዳለ ለማወቅ እስቲ 1 ቆሮንቶስ 13:4-7⁠ን እንመልከት፦

“ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው።”

እስቲ አስበው፦ በትዕግሥትና በደግነት ከሚይዙህ እንዲሁም በምትሳሳትበት ጊዜ ከማይቆጡህ ሰዎች ጋር ስትሆን ምን ይሰማሃል?

“ፍቅር አይቀናም።”

እስቲ አስበው፦ ሌሎች በጣም ሲጠራጠሩህ ወይም ሲመቀኙህ ምን ይሰማሃል?

ፍቅር “የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም።”

እስቲ አስበው፦ አመለካከትህን ከሚያከብሩና ‘እኔ ያልኩት ካልሆነ’ ከማይሉ ሰዎች ጋር ስትሆን ምን ይሰማሃል?

“ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም።”

እስቲ አስበው፦ አምላክ፣ የበደሉት ሰዎች በድርጊታቸው ሲጸጸቱ እነሱን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ ነው። “እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤ ለዘላለምም ቂም አይዝም።” (መዝሙር 103:9) ያስቀየምነው ሰው ይቅርታ ሲያደርግልን እንደሰታለን። እንግዲያው እኛም ሰዎች ሲያስቀይሙን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ እንሁን።—መዝሙር 86:5

“ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም።”

እስቲ አስበው፦ ሌሎች በደረሰብን መጥፎ ነገር ሲደሰቱ እናዝናለን። እኛም የበደሉን ሰዎች እንኳ ችግር ሲገጥማቸው ልንደሰት አይገባም።

የአምላክን በረከት ለማግኘት ለሁሉም ዓይነት ሰዎች በእነዚህ መንገዶች ፍቅር ማሳየት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ የምንችልበት አንዱ መንገድ የተቸገሩትን መርዳት ነው።