በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው?

ዓለምን እየተቆጣጠረ ያለው ማን ነው?

ማን ይመስልሃል?

  • አምላክ?

  • የሰው ልጆች?

  • ወይስ ሌላ አካል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“መላው ዓለም ግን በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።”—1 ዮሐንስ 5:19

አዲስ ዓለም ትርጉም “የአምላክ ልጅ የተገለጠው የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።”—1 ዮሐንስ 3:8

ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው?

ዓለም በችግር የተሞላው ለምን እንደሆነ አሳማኝ ምክንያት ታገኛለህ።—ራእይ 12:12

የተሻለ ዓለም ይመጣል ብሎ ለማመን የሚያስችል ምክንያት ታገኛለህ።—1 ዮሐንስ 2:17

መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ነገር ላይ እምነት መጣል እንችላለን?

አዎ፣ ቢያንስ ሦስት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፦

  • የሰይጣን አገዛዝ ይጠፋል። ይሖዋ የሰውን ዘር ከሰይጣን ቁጥጥር ነፃ ለማውጣት ወስኗል። ይሖዋ ‘ዲያብሎስን እንዳልነበረ ለማድረግና’ ሰይጣን ያደረሰውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ ወደ ቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ቃል ገብቷል።—ዕብራውያን 2:14

  • አምላክ ዓለምን እንዲገዛ ኢየሱስ ክርስቶስን መርጦታል። ኢየሱስ ጨካኝና ራስ ወዳድ ከሆነው የዚህ ዓለም ገዢ ፈጽሞ የተለየ ነው። አምላክ የኢየሱስን አገዛዝ አስመልክቶ ሲናገር “ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤ . . . ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል” ብሏል።—መዝሙር 72:13, 14

  • አምላክ ሊዋሽ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ ‘አምላክ ሊዋሽ እንደማይችል’ በግልጽ ይናገራል። (ዕብራውያን 6:18) ይሖዋ አንድ ነገር ለማድረግ ቃል ሲገባ የተፈጸመ ያህል ልንቆጥረው እንችላለን! (ኢሳይያስ 55:10, 11) ስለዚህ “የዚህ ዓለም ገዢ . . . ይባረራል።”—ዮሐንስ 12:31

ምን ይመስልሃል?

የዚህ ዓለም ገዢ ሲወገድ ዓለም ምን ይመስላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ መዝሙር 37:10, 11 እና ራእይ 21:3, 4 ላይ ይገኛል።