በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 01

መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

ሁላችንም ስለ ሕይወት፣ ስለ ሞትና ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተለያዩ ጥያቄዎችን እናነሳለን፤ እንዲሁም መከራ የሚደርስብን ለምን እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን። በተጨማሪም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙን ጉዳዮች ያስጨንቁናል፤ ለምሳሌ ለኑሮ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ማግኘት ወይም የቤተሰባችንን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምንችልበት መንገድ ያሳስበናል። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በአእምሯቸው ውስጥ ለሚፈጠሩ ትላልቅ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ለዕለት ተዕለት ሕይወታቸው የሚጠቅም ምክር እንደያዘም አስተውለዋል። ታዲያ ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ቢማር ጠቃሚ አይመስልህም?

1. መጽሐፍ ቅዱስ ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል?

መጽሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉት ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፦ ሕይወት ያገኘነው እንዴት ነው? የተፈጠርንበት ዓላማ ምንድን ነው? ጥሩ ሰዎች መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው? ሰው ሲሞት ምን ይሆናል? ሰዎች ሰላም ሰፍኖ ማየት ቢፈልጉም ጦርነት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? ወደፊት ምድር ትጠፋ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ላሉ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ጥረት እንድናደርግ ያበረታታናል። ደግሞም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መልስ ማግኘት ችለዋል።

2. መጽሐፍ ቅዱስ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ደስተኛ እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክሮች ይዟል። ለምሳሌ ያህል፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ያስተምራል። ጭንቀትን መቋቋምና በምንሠራው ሥራ ደስተኛ መሆን ስለምንችልበት መንገድ ምክር ይሰጣል። ይህን ጽሑፍ ተጠቅመህ መወያየትህን ስትቀጥል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ምን እንደሚያስተምር ትረዳለህ። ይህም ‘ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ [በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች በሙሉ] ጠቃሚ’ እንደሆኑ እንድትገነዘብ ያደርግሃል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

ይህ ጽሑፍ መጽሐፍ ቅዱስን የሚተካ አይደለም። ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን አንተው ራስህ እንድትመረምር ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በመሆኑም በምዕራፉ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች አውጥተህ እንድታነብና ከምትማረው ነገር ጋር እንድታነጻጽር እናበረታታሃለን።

ጠለቅ ያለ ጥናት

መጽሐፍ ቅዱስ ብዙዎችን የረዳቸው እንዴት እንደሆነ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነና መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለመረዳት የሌሎች እገዛ የሚያስፈልግህ ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

3. መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ ይሰጠናል

መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደ ደማቅ መብራት ነው። ጥሩ ውሳኔዎችን እንድናደርግ እንዲሁም ከፊታችን የሚጠብቀን ነገር ፍንትው ብሎ እንዲታየን ይረዳናል።

መዝሙር 119:105ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • የዚህ ጥቅስ ጸሐፊ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት ነበረው?

  • አንተስ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ?

4. መጽሐፍ ቅዱስ ለጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጠናል

አንዲት ሴት ለበርካታ ዓመታት ሲያስጨንቋት ለነበሩ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ አግኝታለች። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ የታየችው ሴት ምን ጥያቄዎች ነበሯት?

  • መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቷ የጠቀማት እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን እንድንጠይቅ ያበረታታናል። ማቴዎስ 7:7ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለየትኛው ጥያቄህ መልስ ማግኘት ትፈልጋለህ?

5. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ ትችላለህ

ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ያስደስታቸዋል። እንዲህ በማድረጋቸውም የተለያዩ ጥቅሞች እያገኙ ነው። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ የታዩት ወጣቶች፣ በአጠቃላይ ስለ ንባብ ምን አመለካከት አላቸው?

  • መጽሐፍ ቅዱስን ስለ ማንበብ ግን የተለየ አመለካከት ያላቸው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ በውስጡ የያዘው ሐሳብ መጽናኛና ተስፋ እንደሚሰጠን ይናገራል። ሮም 15:4ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው ማጽናኛና ተስፋ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?

6. መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለመረዳት የሌሎች እርዳታ ያስፈልገናል

ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው ከማንበብ በተጨማሪ ከሌሎች ጋር መወያየቱን ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። የሐዋርያት ሥራ 8:26-31ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

ኢትዮጵያዊው ሰው የሚያነበውን ነገር ለመረዳት እርዳታ አስፈልጎት ነበር። በዛሬው ጊዜ በርካታ ሰዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ጋር መወያየታቸው ጠቃሚ እንደሆነ ይሰማቸዋል

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጊዜ ማባከን ነው።”

  • አንተስ ምን ትላለህ?

ማጠቃለያ

መጽሐፍ ቅዱስ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚጠቅም ምክር ይሰጣል፣ ለምናነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይዟል እንዲሁም ማጽናኛና ተስፋ ይሰጠናል።

ክለሳ

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ምክሮች እናገኛለን?

  • መጽሐፍ ቅዱስ ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል?

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ ምን መማር ትፈልጋለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች ለዘመናችን ጠቃሚ የሆኑት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

“ዘመን የማይሽራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች” (መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2018)

መጽሐፍ ቅዱስ ከልጅነቱ ጀምሮ ከአሉታዊ ስሜት ጋር ሲታገል የኖረን ሰው የረዳው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

በሕይወቴ ደስተኛ ሆንኩ (2:53)

መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ለቤተሰብ ሕይወት ጠቃሚ የሆነ ምክር አንብብ።

“ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮች” (ንቁ! ቁጥር 2 2018)

መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ዓለም ገዢ በተመለከተ የያዘው ሐሳብ ከብዙዎች አመለካከት የሚለየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?—ሙሉው ቪዲዮ (3:14)