በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የውድ ሀብት ከተማ “አምላክ ለሰዎች የሰጠውን ስጦታ” ለእይታ አቀረበች

የውድ ሀብት ከተማ “አምላክ ለሰዎች የሰጠውን ስጦታ” ለእይታ አቀረበች

ከሮማኒያ ትልልቅ ከተሞች አንዷ የሆነችው ክሉዥ ናፖካ ‘የውድ ሀብት ከተማ’ በመባል ትታወቃለች። ከሚያዝያ 20 እስከ 24, 2016 በከተማዋ በተካሄደው የጋውዲያሙስ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ላይ የይሖዋ ምሥክሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ እሴቶች ጎልተው እንዲታዩ አድርገዋል። አውደ ርዕዩ በተካሄደበት ቦታ ኪዮስክ አቁመው ስለተለያዩ የድርጅቱ ቪዲዮዎች፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻችንና ለእይታ ስላቀረቧቸው መጽሐፍ ቅዱሶች ለማወቅ ጉጉት ላደረባቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ገለጻ አድርገዋል።

ብዙ ትምህርት ቤቶች አውደ ርዕዩን ለመጎብኘት ትምህርታዊ ጉዞ ያደረጉ ሲሆን አስተማሪዎችም ተማሪዎቻቸውን ይዘው በመምጣት የይሖዋ ምሥክሮች ጽሑፎቻቸውን ለእይታ ያቀረቡበትን ኪዮስክ እንዲጎበኙ አድርገዋል። ተማሪዎቹ የይሖዋ ወዳጅ ሁን በሚል ርዕስ የቀረቡትን ተከታታይ የአኒሜሽን ቪዲዮዎች ማየታቸው በጣም ያስደሰታቸው ሲሆን አብዛኞቹም የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ መጽሐፌ የተባለው መጽሐፍና ልጆቻችሁን አስተምሩ የተባለው ብሮሹር እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። የአኒሜሽን ቪዲዮዎቹን ያየች አንዲት የሕፃናት እንክብካቤ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባዋ “ለልጆቹ የአሻንጉሊት ፊልሞቹን በሙሉ እንድናሳያቸው [የ​www.pr418.com​ን] አድራሻ በማስታወሻችን ጽፈን መያዝ ያስፈልገናል” በማለት ተናግራለች።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች በታብሌቶች ላይ በተመለከቷቸው የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን ቪዲዮዎች በጣም ተደንቀዋል። ከቀረቡት ቪዲዮዎች መካከል እውነተኛ ፍቅር ነው ወይስ የወረት? እንዲሁም ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን እና ቡጢ ሳትሰነዝር ጉልበተኞችን ማሸነፍ የሚሉት ይገኙባቸዋል።

አንድ የኦርቶዶክስ ቄስና ሚስታቸው የይሖዋ ምሥክሮችን ኪዮስክ በተደጋጋሚ የጎበኙ ሲሆን አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስን እና የተለያዩ ብሮሹሮችን ወስደዋል። ቄሱ “የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ማውጫ” በሚለው የዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ገጽታና ተርጓሚዎቹ በተጠቀሙባቸው በርካታ እምነት የሚጣልባቸው ምንጮች እንደተደነቁ ተናግረዋል። ቄሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጨማሪ ውይይት ማድረግ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ስልክ ቁጥራቸውን ለይሖዋ ምሥክሮቹ ሰጥተዋል።

የቄሱ ሚስት ለልጆች የሚሆን ነገር የሚገኘው በየትኛው የድረ ገጹ ክፍል ላይ እንደሆነ የጠየቀች ሲሆን “ልጆች” በሚለው ክፍል ላይ ልታገኘው እንደምትችል ተነግሯታል። ከዚያም እውነቱን ተናገር የሚለውን ቪዲዮ አይታ በጣም ተደስታለች። ባለቤቷም ቪዲዮውንና ሌሎቹን የድረ ገጹን ገጽታዎች ከቃኙ በኋላ ድረ ገጹን “አምላክ ለሰዎች የሰጠው ስጦታ” ሲሉ ጠርተውታል።