በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ተብላችሁ የምትጠሩት ለምንድን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ተብላችሁ የምትጠሩት ለምንድን ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ የግል ስም ይሖዋ ነው። (ዘፀአት 6:3 የ1879 ትርጉም) አንድ ሰው ያመነበትን አመለካከት ወይም እውነት ለሌሎች የሚናገር ከሆነ ደግሞ ምሥክር ይባላል።

 በመሆኑም የይሖዋ ምሥክሮች የሚለው መጠሪያ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ስለሆነው ስለ ይሖዋ እውነቱን የምንናገር ክርስቲያኖች መሆናችንን በቡድን ደረጃ ለይቶ ያሳውቀናል። (ራእይ 4:11) በአኗኗራችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘነውን እውቀት ለሌሎች በማካፈል ለሰዎች እንመሠክራለን።​—ኢሳይያስ 43:10-12፤ 1 ጴጥሮስ 2:12