በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ማጥኛ ጽሑፍ

እነዚህን የማጥኛ ጽሑፎች አውርድና ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? ከተባለው መጽሐፍ ጋር ተጠቀምባቸው። እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛዎች የምታምንባቸውን ነገሮች ለመመርመር፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለመረዳት እና ለሌሎች ለማስረዳት ይጠቅሙሃል።

ምዕራፍ 1

አምላክን በተመለከተ ትክክለኛው ትምህርት የቱ ነው? (ክፍል 1)

አንድ ሰው ‘አምላክ መጥፎ ሰዎችን መከራ እንዲደርስባቸው በማድረግ ይቀጣቸዋል’ ቢልህ ምን መልስ ትሰጠዋለህ?

ምዕራፍ 2

መጽሐፍ ቅዱስ—አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠው መጽሐፍ (ክፍል 1)

መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ናቸው፤ ታዲያ ‘አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠው መጽሐፍ’ ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 2

መጽሐፍ ቅዱስ—አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠው መጽሐፍ (ክፍል 2)

ብዙ ሰዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛ መጽሐፍ መሆኑን እንዲያምኑ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ?

ምዕራፍ 3

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው? (ክፍል 1)

የአምላክ ዓላማ፣ የሰው ልጆች አሁን ባለው ዓይነት ሁኔታ እንዲኖሩ ነበር?

ምዕራፍ 3

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው? (ክፍል 2)

የአምላክ ዓላማ ምድርን ገነት ማድረግ ከሆነ በአሁኑ ጊዜ ይህ ዓላማው ያልተፈጸመው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 3

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው? (ክፍል 3)

የሰው ልጆች በምድር ላይ ያሉትን ችግሮች በሙሉ ሊያስወግዱ ይችላሉ?

ምዕራፍ 4

ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? (ክፍል 1)

አንድ ሰው፣ ኢየሱስ እንዲሁ ጥሩ ነገር ሠርቶ ያለፈ ሰው እንጂ ከዚያ የበለጠ ቦታ እንደሌለው ቢነግርህ ምን ምላሽ ትሰጣለህ?

ምዕራፍ 4

ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? (ክፍል 2)

አንድ ሰው፣ ኢየሱስ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር እኩል እንደሆነ ቢነግርህ ምን ምላሽ ትሰጣለህ?

ምዕራፍ 5

ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ (ክፍል 1)

መዳን በሥራ ሊገኝ የሚችል ነገር ነው?

ምዕራፍ 5

ቤዛው—ከሁሉ የላቀ የአምላክ ስጦታ (ክፍል 2)

በሺዎች ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት የኖረ አንድ ሰው ሞት፣ በዛሬው ጊዜ በአንተ ሕይወት ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 6

ሙታን የት ናቸው? (ክፍል 1)

የሚኖሩበት ሌላ ዓለም አለ? ገሃነም ገብተው እየተቃጠሉ ነው?

ምዕራፍ 6

ሙታን የት ናቸው? (ክፍል 2)

ሞት ተፈጥሯዊ የሕይወት ክፍል ነው?

ምዕራፍ 7

በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ያላቸው እውነተኛ ተስፋ (ክፍል 1)

ማዘንህ በትንሣኤ ተስፋ ላይ እምነት እንደሌለህ ያሳያል?

ምዕራፍ 7

በሞት የተለዩህ የምትወዳቸው ሰዎች ያላቸው እውነተኛ ተስፋ (ክፍል 2)

የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ ብሎ ማመን ለሚከብደው ሰው ምን መልስ መስጠት ትችላለህ?

ምዕራፍ 8

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (ክፍል 1)

በሰማይ ብዙ ታማኝ መላእክት እያሉ አምላክ ከሰው ልጆች መካከል በሰማይ የሚገዙ ነገሥታት የመረጠው ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 8

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (ክፍል 2)

የአምላክ መንግሥት እስከ ዛሬ ምን አከናውኗል? ወደፊትስ ምን ያከናውናል?

ምዕራፍ 9

የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ ነው? (ክፍል 1)

አንዳንዶች በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥ እንደምንኖር ማመን ይከብዳቸዋል። ወደዚህ ሥርዓት መደምደሚያ እንደተቃረብን እርግጠኛ እንድትሆን የሚያስችልህ ምንድን ነው?

ምዕራፍ 9

የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” ውስጥ ነው? (ክፍል 2)

መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚፈጸሙ አዎንታዊ ክንውኖች እንዳሉ ይናገራል።

ምዕራፍ 10

መንፈሳዊ ፍጡራንሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት ነው? (ክፍል 1)

መላእክት በእርግጥ አሉ? መጥፎ መላእክትስ አሉ? መልሱን ለማወቅ ይህን የማጥኛ ጽሑፍ ተጠቀም።

ምዕራፍ 10

መንፈሳዊ ፍጡራን—ሊጠቅሙን ወይም ሊጎዱን የሚችሉት እንዴት ነው? (ክፍል 2)

ከመንፈሳዊው ዓለም ጋር ለመገናኘት መሞከር ምን ችግር አለው?

ምዕራፍ 11

አምላክ በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው? (ክፍል 1)

አምላክ ሁሉን ቻይ ከሆነ፣ በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሰው መከራ ሁሉ ተጠያቂው እሱ ነው ማለት አይደለም?

ምዕራፍ 11

አምላክ በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምንድን ነው? (ክፍል 2)

ቅዱሳን መጻሕፍት ለዚህ ከባድ ጥያቄ ግልጽና አጥጋቢ መልስ ይሰጣሉ።

ምዕራፍ 12

አምላክን በሚያስደስት መንገድ መኖር (ክፍል 1)

የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ? ምን ብለህ እንደምታምንና እንዲህ ብለህ የምታምንበትን ምክንያት እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር ተመልከት።

ምዕራፍ 12

አምላክን በሚያስደስት መንገድ መኖር (ክፍል 2)

ሰይጣን የሚያደርስብንን ፈተናዎች ተቋቁመን አምላክን ማስደሰት እንችላለን?

ምዕራፍ 12

አምላክን በሚያስደስት መንገድ መኖር (ክፍል 3)

ሕይወትህን ከመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ጋር በሚስማማ መንገድ መምራት ጥረት ይጠይቃል። እንዲህ ያለ ጥረት ማድረጋችን ጥቅም አለው?

ምዕራፍ 13

አምላክ ለሕይወት ያለው ዓይነት አመለካከት አለህ? (ክፍል 1)

ሕይወት አምላክ የሰጠን ስጦታ ነው። ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ሕይወት አክብሮት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 13

አምላክ ለሕይወት ያለው ዓይነት አመለካከት አለህ? (ክፍል 2)

ይህ ማጥኛ ጽሑፍ የደምን አጠቃቀምና ደም መውሰድን በተመለከተ እምነትህን እንድትመረምር ብቻ ሳይሆን እምነትህን ለሌሎች ማስረዳት እንድትችልም ይረዳሃል።

ምዕራፍ 14

የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? (ክፍል 1)

አስደሳች የትዳር ሕይወት ለመምራት ቁልፉ ምንድን ነው? እምነትህን ፈትሽ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምር መርምር እንዲሁም እምነትህን ለሌሎች እንዴት ማስረዳት እንደምትችል በዚህ የማጥኛ ጽሑፍ አማካኝነት ተለማመድ።

ምዕራፍ 14

የቤተሰብህን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? (ክፍል 2)

ወላጆችም ሆኑ ልጆች ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ በመከተል ጥቅም ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው? የምታምንበትን ነገር እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጉዳዩ የሚናገረውን ነገር መርምር።

ምዕራፍ 15

አምላክ የሚቀበለው አምልኮ (ክፍል 1)

ሁሉም ሃይማኖቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው? ካልሆነ እውነተኛውን ሃይማኖት ለይተህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? እምነትህንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚያስተምር መርምር።

ምዕራፍ 15

አምላክ የሚቀበለው አምልኮ (ክፍል 2)

በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት በእሱ ማመን ብቻውን በቂ ነው? ወይስ አምላክ ከሚያመልኩት ሰዎች የሚጠብቅባቸው ሌላም ነገር አለ?

ምዕራፍ 16

ከእውነተኛው አምልኮ ጎን ቁም (ክፍል 1)

ልደትንና ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን ማክበር እንዲሁም ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀም በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው? ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊረዱን የሚችሉት የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ናቸው?

ምዕራፍ 16

ከእውነተኛው አምልኮ ጎን ቁም (ክፍል 2)

ስለ እምነትህ ለሌሎች በዘዴ ማስረዳትና ለሌሎች ሰዎች አመለካከት አክብሮት እንዳለህ ማሳየት የምትችለው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 17

በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር (ክፍል 1)

የአምላክ ወዳጅ መሆን የምትችለው እንዴት ነው? አምላክ ጸሎትህን እንደሚሰማ እንዴት ማወቅ ትችላለህ?

ምዕራፍ 17

በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር (ክፍል 2)

መጽሐፍ ቅዱስ እንዴትና መቼ መጸለይ እንዳለብን የሚናገረውን ሐሳብ ተመልከት።

ምዕራፍ 17

በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር (ክፍል 3)

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ለጸሎታችን መልስ የሚሰጠን በተለያየ መንገድ እንደሆነ ይናገራል። ታዲያ ለጸሎታችን መልስ የሚሰጠን እንዴትና መቼ ሊሆን ይችላል?

ምዕራፍ 18

ጥምቀትና ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና (ክፍል 1)

አንድ ክርስቲያን መጠመቅ ያለበት ለምንድን ነው? ክርስቲያኖች ለመጠመቅ የሚያነሳሳቸው ነገር ምንድን ነው?

ምዕራፍ 18

ጥምቀትና ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና (ክፍል 2)

አንድ ሰው ራሱን ለአምላክ ከመወሰኑ በፊት ሊወስዳቸው የሚገቡ እርምጃዎች ምንድን ናቸው? ራሱን ለአምላክ መወሰኑ፣ ከዚያ በኋላ በሚያደርጋቸው ሌሎች ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው?

ምዕራፍ 18

ጥምቀትና ከአምላክ ጋር ያለህ ዝምድና (ክፍል 3)

ራሱን የወሰነ አንድ ክርስቲያን ምን ይጠበቅበታል? እንዲሁም አምላክን ከልብ የሚወዱ ሰዎች ለእሱ የገቡትን ቃል ጠብቀው መኖር እንደሚችሉ እርግጠኞች መሆን የሚችሉት ለምንድን ነው?

ምዕራፍ 19

ከአምላክ ፍቅር አትውጣ (ክፍል 1)

ከአምላክ ጋር የመሠረትከውን የጠበቀ ዝምድና እስከ መጨረሻው ይዘህ መቀጠል የምትችለው እንዴት ነው? ይህ ማጥኛ ጽሑፍ የምታምንበትን ነገር ለመመርመርና እምነትህን ለሌሎች ለማስረዳት ይረዳሃል።

ምዕራፍ 19

ከአምላክ ፍቅር አትውጣ (ክፍል 2)

ስለ አምላክ እውነቱን ከተማርክ በኋላ ወደ እሱ ይበልጥ እንድትቀርብ የሚረዳህ ምንድን ነው? ለአምላክ ያለህ ፍቅር ምንጊዜም ጠንካራ እንዲሆን ማድረግ የምትችለውስ እንዴት ነው?