በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አምላክ የሚኖረው በአንድ የተወሰነ ቦታ ነው?

አምላክ የሚኖረው በአንድ የተወሰነ ቦታ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አዎን። አምላክ የሚኖረው በሰማይ ነው። ቀጥሎ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እስቲ ልብ በል፦

 ንጉሥ ሰለሞን ወደ አምላክ ሲጸልይ “አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ” ብሏል።—1 ነገሥት 8:43

 ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “በሰማያት የምትኖር አባታችን” ብለው ወደ አምላክ እንዲጸልዩ ደቀ መዛሙርቱን አስተምሯቸዋል።—ማቴዎስ 6:9

 ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ “በአምላክ ፊት ይታይ ዘንድ በቀጥታ ወደ ሰማይ ገብቷል።”—ዕብራውያን 9:24

 እነዚህ ጥቅሶች፣ ይሖዋ አምላክ ሁሉም ቦታ የሚገኝ ኃይል ሳይሆን የራሱ ማንነት እንዳለው እንዲሁም መኖሪያው በሰማይ ብቻ እንደሆነ ይጠቁማሉ።