በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሕይወት የያዘው ዘገባ ትክክለኛ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሕይወት የያዘው ዘገባ ትክክለኛ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ሉቃስ ስለ ኢየሱስ ሕይወት የጻፈውን ዘገባ አስመልክቶ “ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው አንስቶ በጥንቃቄ [መረመርኩ]” ብሏል።—ሉቃስ 1:3

 በኢየሱስ ዘመን የኖሩት ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ሕይወት የጻፏቸው የወንጌል ዘገባዎች በአራተኛው መቶ ዘመን አካባቢ ለውጥ እንደተደረገባቸው አንዳንዶች ይናገራሉ።

 ይሁንና በ20ኛው መቶ ዘመን መባቻ ላይ በግብፅ የዮሐንስ ወንጌልን የያዘ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ቁራጭ ተገኘ። ይህ ቁራጭ አሁን ፓፒረስ ራይላንድስ 457 (P52) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በማንቼስተር፣ እንግሊዝ በጆን ራይላንድስ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ ይገኛል። በዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ በዮሐንስ 18:31-33, 37, 38 ላይ የሚገኘውን ክፍል ይዟል።

 እስከ ዛሬ ከተገኙ በእጅ የተገለበጡ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ቅጂዎች መካከል ይህ ቁራጭ ጥንታዊው ነው። ይህ ቅጂ የተጻፈው በ125 ዓ.ም. ገደማ ይኸውም የመጀመሪያው ጽሑፍ ከተዘጋጀ ከ25 ዓመት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ብዙ ምሁራን ያምናሉ። በዚህ ቁራጭ ላይ የተገኘው ጽሑፍ ከዚያ በኋላ በተገለበጡ ቅጂዎች ላይ ከሚገኘው ጋር ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል።