በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ

የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ

“መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” (እንግሊዝኛ) የተባለው የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ መጽሐፍ ቅዱስን ጠለቅ ብለህ ለማጥናት የሚረዱ ዝርዝር መረጃዎች ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ብዙ ቦታዎች፣ ከተሞችና አገሮች ተጠቅሰዋል። ይህን አትላስ ተጠቅመህ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የምታነበውና የምታጠናው ነገር ሕያው እንዲሆንልህ ማድረግ ትችላለህ። ይህ ጽሑፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ክንውኖች የተፈጸሙበትን ቦታ በዓይነ ሕሊናህ ለመሣልና የት እንደሚገኙ ለማወቅ ይረዳሃል። በተጨማሪም የቦታዎቹ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በተጠቀሱት ክንውኖች ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ ግንዛቤ ይሰጥሃል።

“መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” የተባለው አትላስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የተለያዩ ቦታዎችን የሚያሳዩ ባለቀለም ካርታዎችና ሰንጠረዦች ይዟል። በተጨማሪም የተለያዩ ሥዕላዊ መግለጫዎች፣ በኮምፒውተር የተሠሩ ምስሎችና ሌሎች ገጽታዎች አሉት፤ እነዚህ ሁሉ በግልህ የምታደርገውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስደሳች ያደርጉልሃል።

ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ በመጠቀም የሚከተሉትን መረጃዎች ማግኘት ትችላለህ፦

  • አብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ ያደረጓቸው ጉዞዎች

  • እስራኤላውያን ከግብፅ ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር ሲጓዙ የሄዱበት መንገድ

  • የእስራኤል ጠላት የሆኑ ብሔራት ከእስራኤል አንጻር የነበሩበት ቦታ

  • ኢየሱስ በአገልግሎቱ ወቅት ያካለላቸው አካባቢዎች

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ታላላቅ ግዛቶች ለምሳሌ ባቢሎን፣ ግሪክና ሮም ተቆጣጥረውት የነበረው ክልል ስፋት

ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ (እንግሊዝኛ) ኢንተርኔት ላይ በነፃ ማግኘት ትችላለህ።