ሚያዝያ 23, 2024
ሩሲያ
ይሖዋን ማገልገል ትልቅ መብት ነው
በኡድሙርቲያን ሪፑብሊክ፣ በኢዢፍስክ ከተማ የሚገኘው የፐርቮማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዬቭጌኒ ስቴፋኒዲን እና በወንድም አሌክሳንደር ቮትያኮቭ ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
እንደ አሌክሳንደር እና ዬቭጌኒ ሁሉ እኛም በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ለይሖዋ ‘ያለፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ’ መቻል ትልቅ መብት እንደሆነ ይሰማናል።—ሉቃስ 1:74, 75
የክሱ ሂደት
ሚያዝያ 14, 2021
የደህንነት ሰዎች የዬቭጌኒን ቤት ፈተሹ
ታኅሣሥ 13, 2022
አሌክሳንደር እና ዬቭጌኒ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው
ታኅሣሥ 14, 2022
ፖሊሶች የሁለቱንም ቤቶች ፈተሹ። አሌክሳንደር ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ። ዬቭጌኒ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት
ታኅሣሥ 15, 2022
አሌክሳንደር ከጣቢያ ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ ተደረገ
ሰኔ 9, 2023
አሌክሳንደር ከቁም እስር ተፈታ፤ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት
ነሐሴ 17, 2023
ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ