በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ሰርጌ አሺክሚን፣ ወንድም ማክሲም ዴሬንድዬቭ እና ወንድም አሌክሳንደር ኩቲን

ሐምሌ 8, 2022 | የታደሰው፦ ግንቦት 13, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ጸሎት ብርታት ሰጥቷቸዋል

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ታሰሩ | ጸሎት ብርታት ሰጥቷቸዋል

ግንቦት 13, 2024 በኢዢፍስክ የሚገኘው የፐርቮማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ሰርጌ አሺክሚን፣ በወንድም ማክሲም ዴሬንድዬቭ እና በወንድም አሌክሳንደር ኩቲን ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሦስቱም የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል። ከፍርድ ቤት በቀጥታ ወህኒ ወርደዋል።

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 14, 2021

    የፌዴራል ደህንነት አባላት ቢያንስ 12 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ። ሰርጌ ለሰባት ሰዓታት ምርመራ ተደረገበት። ማክሲም እና አሌክሳንደር ተይዘው ጣቢያ ተወሰዱ

  2. ሚያዝያ 15, 2021

    ማክሲም እና አሌክሳንደር ማረፊያ ቤት እንዲገቡ ተደረጉ

  3. ሚያዝያ 29, 2021

    አሌክሳንደር ከማረፊያ ቤት ተለቀቀ

  4. ግንቦት 14, 2021

    አሌክሳንደር የቁም እስረኛ ተደረገ

  5. ሐምሌ 9, 2021

    ማክሲም ከማረፊያ ቤት ተፈትቶ የቁም እስረኛ ተደረገ

  6. መጋቢት 14, 2022

    የክሱ ሂደት በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

አጭር መግለጫ

ወንድሞቻችን፣ ይሖዋ “እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” በማለት በገባው ቃል በመተማመን የሚደርስባቸውን ግፍ እየተጋፈጡ ነው።—ኢሳይያስ 43:5