በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ እህት ልዩቦቭ ጋሊትሲና፣ ወንድም ጋሬጊን ኻቻቱርያን እና ወንድም ጌቮርግ ዬሪትስያን

ሚያዝያ 8, 2024
ሩሲያ

ማረፊያ ቤት ውስጥ የይሖዋን እንክብካቤ መቅመስ

ማረፊያ ቤት ውስጥ የይሖዋን እንክብካቤ መቅመስ

በሮስቶቭ ክልል የሚገኘው የኖቮቼርካስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በእህት ልዩቦቭ ጋሊትሲና፣ በወንድም ጋሬጊን ኻቻቱርያን እና በወንድም ጌቮርግ ዬሪትስያን ክስ ላይ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባቸው የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።

አጭር መግለጫ

ተቃዋሚዎቻችን ጉዳት ሊያደርሱብን ቢያስቡም ይሖዋ ታማኝ አገልጋዮቹን መባረኩን እንደሚቀጥልና “ነገሩን ለመልካም [እንደሚያደርገው]” እንተማመናለን።​—ዘፍጥረት 50:20

የክሱ ሂደት

  1. ነሐሴ 11, 2022

    ልዩቦቭ፣ ጋሬጊን እና ጌቮርግ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው። ቤቶቻቸው ተፈተሹ። ጋሬጊን እና ጌቮርግ ጣቢያ ተወሰዱ

  2. ነሐሴ 12, 2022

    ጋሬጊን እና ጌቮርግ ማረፊያ ቤት ገቡ

  3. ነሐሴ 16, 2022

    ልዩቦቭ ጣቢያ ተወሰደች

  4. ነሐሴ 17, 2022

    ልዩቦቭ ማረፊያ ቤት ገባች

  5. መስከረም 20, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ

  6. ታኅሣሥ 25, 2023

    ልዩቦቭ ከማረፊያ ቤት ተለቀቀች፤ የቁም እስረኛ ሆነች

a b ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት ወንድም ጋሬጊን እና ወንድም ጌቮርግ ማረፊያ ቤት ስለነበሩ አስተያየታቸውን ማግኘት አልተቻለም