በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘እውነተኛው ሕይወት’

‘እውነተኛው ሕይወት’

አውርድ፦

  1. 1. በጠራ ሰማይ፣ ፈንጥቃ ፀሐይ፣ ፍክት ባለ ማለዳ፤

    መስኩ አብቦ፣ ልምላሜ ጠግቦ፣

    ኑ እንሂድ ወደ ሜዳ።

    እንደ ልጅ ቦርቅ ይለኛል፤ ቦርቅ፣ ተነሳ፤

    ምድር በጸጋው ተሞላች፣ ባምላክ ስጦታ።

    (ቅድመ አዝማች)

    የዛሬው ሊያልፍ ነው፣ ሊረሳ።

    (አዝማች)

    ያኔማ ለደስታችን ምን ጥግ አለው፤ ሲሸኝ ይህ ጨለማ።

    እውነተኛው ሕይወት አይጠገብ፤ ልናይ ነው ገና፤

    አለ ገና!

  2. 2. ወደ ሥራ፣ ሁሉም ሰው ይጠራ፤ ባዲስ ጉልበት እንትጋ።

    ሳቅ፣ ጨዋታ፣ እዚያም እዚህም ደስታ፤ የለም አንዳች ’ሚያሰጋ።

    ሐዘን በሐሴት ተተካ፤ ሰላም ሁሉ ጋ!

    መኖር ጣ’ሙ ይህ ነው ለካ፤ ልባችን ረካ።

    (አዝማች)

    ያኔማ ለደስታችን ምን ጥግ አለው፤ ሲሸኝ ይህ ጨለማ።

    እውነተኛው ሕይወት አይጠገብ፤ ልናይ ነው ገና፤

    አለ ገና!

    (መሸጋገሪያ)

    እስከዚያው ተስፋው ተቀርጿል ባሳቤ ተስሎ፤

    አይቀርም፣ እውን ይሆናል በቅርቡ፤ ቀን ቆጥሮ።

    (አዝማች)

    ያኔማ ለደስታችን ምን ጥግ አለው፤ ሲሸኝ ይህ ጨለማ።

    እውነተኛው ሕይወት አይጠገብ፤ ልናይ ነው ገና!

    (አዝማች)

    ያኔማ ለደስታችን ምን ጥግ አለው፤ ሲሸኝ ይህ ጨለማ።

    እውነተኛው ሕይወት አይጠገብ፤ ልናይ ነው ገና፤

    አለ ገና!

    (መደምደሚያ)

    ልናይ ነው፤ ልናይ ነው፤

    አለ ገና!

    ልናይ ነው፤ ልናይ ነው፤

    አለ ገና!

    ልናይ ነው፤ ልናይ ነው፤

    አለ ገና!

    ልናይ ነው፤ ልናይ ነው፤

    አለ ገና!