በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከግራ ወደ ቀኝ፦ ወንድም ዩሪ ኮሎቲንስኪ፣ ወንድም ሚካይል ሬሼትኒኮቭ እና ወንድም አናቶሊ ሳሪቼቭ

መጋቢት 27, 2024 | የታደሰው፦ ግንቦት 13, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ጥፋተኛ ተባሉ | ልበ ሙሉ፣ ዝግጁና አዎንታዊ ሆኖ መጽናት

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ጥፋተኛ ተባሉ | ልበ ሙሉ፣ ዝግጁና አዎንታዊ ሆኖ መጽናት

ግንቦት 13, 2024 በአልታይ ግዛት፣ በባርናውል ከተማ የሚገኘው የሌኒንስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ በወንድም ዩሪ ኮሎቲንስኪ፣ በወንድም ሚካይል ሬሼትኒኮቭ እና በወንድም አናቶሊ ሳሪቼቭ ላይ የጥፋተኝነት ብይን አስተላልፏል። ሦስቱም የሁለት ዓመት ከሦስት ወር የገደብ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት ወህኒ አይገቡም።

አጭር መግለጫ

በይሖዋ ላይ እምነት በመጣልና በእሱ በመመካት ረገድ ግሩም ምሳሌ የሚሆኑ እንዲህ ያሉ ወንድሞች ስላሉን አመስጋኞች ነን። የይሖዋ ታማኝ ፍቅርና እንክብካቤ እንደማይለያቸው ሙሉ እምነት አለን።​—መዝሙር 25:10

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 25, 2021

    ሚካይል የክስ ፋይል ተከፈተበት

  2. ግንቦት 27, 2021

    የሚካይል ቤት ተፈተሸ። እሱና አንቶኒና ምርመራ ተደረገባቸው። ሚካይል የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  3. ጥቅምት 6, 2022

    አናቶሊ እና ዩሪ የክስ ፋይል ተከፈተባቸው፤ ከዚያም ክሳቸው በሚካይል መዝገብ እንዲካተት ተደረገ

  4. ጥቅምት 7, 2022

    አናቶሊ እና ዩሪ የጉዞ ገደቦች ተጣሉባቸው

  5. ጥር 19, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ