በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያኖች ናቸው?

የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያኖች ናቸው?

 አዎ። ክርስቲያኖች ነን የምንልባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦

  •   የኢየሱስን ትምህርቶች ለመከተልና ባሕርያቱን ለማንጸባረቅ ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን።​—1 ጴጥሮስ 2:21

  •   ከኢየሱስ በስተቀር “ልንድንበት የሚገባ ከሰማይ በታች ለሰዎች የተሰጠ ሌላ ስም” ስለሌለ ለመዳን ቁልፉ ኢየሱስ እንደሆነ እናምናለን።​—የሐዋርያት ሥራ 4:12

  •   አንድ ሰው የይሖዋ ምሥክር የሚሆነው በኢየሱስ ስም ሲጠመቅ ነው።​—ማቴዎስ 28:18, 19

  •   ጸሎታችንን የምናቀርበው በኢየሱስ ስም ነው።​—ዮሐንስ 15:16

  •   ኢየሱስ በሰው ዘር ሁሉ ላይ ራስ እንዲሆን ማለትም ሥልጣን እንዲኖረው የተሾመ መሆኑን እናምናለን።​—1 ቆሮንቶስ 11:3

 ይሁንና ክርስቲያን ተብለው ከሚጠሩት ሌሎች ሃይማኖቶች የምንለይባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ የሥላሴ ክፍል ሳይሆን የአምላክ ልጅ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምር እናምናለን። (ማቴዎስ 16:16፤ ማርቆስ 12:29) ነፍስ አትሞትም በሚለው ትምህርት አናምንም፤ እንዲሁም አምላክ ሰዎችን በገሃነመ እሳት ለዘላለም ያሠቃያቸዋል የሚለው ትምህርት ጨርሶ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት እንደሌለው እናምናለን። የሃይማኖት መሪዎች ከሌሎች ከፍ ብለው እንዲታዩ የሚያደርጓቸው ማዕረጎች ሊሰጧቸው ይገባል በሚለው ሐሳብም አንስማማም።​—መክብብ 9:5፤ ሕዝቅኤል 18:4፤ ማቴዎስ 23:8-10